የጥራት ፖሊሲ | Quality Policy
ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ (ኮፖኮ) በ2023 በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ኮሌጆች ግንባር ቀደም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመሆን ራዕይ ያለው እና ቀጣይነት ባለው የማሻሻያ ስራዎች አማካኝነት ተልዕኮውን ለመወጣት ያለማቋረጥ ጥረት ያደርጋል። በተጨማሪም ኮሌጁ ከደንበኞች ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የውጤት ተኮር ስልጠና በመስጠት ሙያዊ ክህሎቶችን ከስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ጋር በማዋሃድ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ ሽግግር እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎትን ይሰጣል። ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት (QMS) ን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ሲሆን የደንበኞቹን ፍላጎቶች እና የሚጠበቁ አገልግሎቶችን በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በሰዓቱ በማቅረብ ህጋዊ እና ተፈፃሚነት ያላቸውን የህግ መስፈርቶች መከበራቸውን ያረጋግጣል፡፡ ኮሌጁ በመደበኛ ግምገማዎች ላይ በመንተራስ የአስተዳደር መዋቅሩን ለማጎልበት እና የስልጠና ፕሮግራሞቹን ያለማቋረጥ ለማሻሻል ወቅታዊ እና ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳል።
Kombolcha Polytechnic College (KPC) aspires to become one of the leading polytechnic college in East Africa by 2030, continuously striving to fulfill its mission through improvement initiatives. KPC provides result-oriented training tailored to customer needs, integrating professional knowledge with entrepreneurial thinking, developing a qualified workforce, and supporting micro and small enterprises through technology transfer and industry extension services based on customer needs in four extension packages. KPC is dedicated to implementing ISO 9001:2015 QMS to consistently meet and exceed customer expectations in terms of quality, affordability, and timely delivery while ensuring compliance with statutory and applicable legal requirements. Through regular evaluations, KPC will take timely and appropriate measures to enhance its management structure and continuously improve its training programs.